ቢዝነስ

አቶ ሙስጠፌ በ250 ሚሊየን ብር የተገነባውን የመኪና መገጣጠሚያ ፋብሪካ መረቁ

By ዮሐንስ ደርበው

May 14, 2024

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 6፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የሶማሌ ክልል ርዕሰ መሥተዳድር ሙስጠፌ መሐመድ በ250 ሚሊየን ብር በጅግጅጋ ከተማ የተገነባውን የመኪና መገጣጠሚያ ፋብሪካ መርቀው ሥራ አስጀመሩ፡፡

ርዕሰ መሥተዳድሩ በዚሁ ወቅት ባደረጉት ንግግር÷ ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ የግል ባለሀብቱ በክልሉ እያከናወናቸው የሚገኙ የልማት ስራዎች አበረታች ናቸው ብለዋል።

መሰል የኢንቨስትመንት ስራዎች የውጪ ምንዛሬ ወጪን ከመቀነስ ባለፈ ለዜጎች የስራ ዕድሎችን የሚፈጥሩ መሆናቸውንም አንስተዋል፡፡

መንግስት ለግሉ ዘርፍ የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥልም አረጋግጠዋል።

በቀን እስከ 10 መኪና የመገጣጠም አቅም ያለው ፋብሪካው÷ አሁን ላይ ለ100 ሠራተኞች የሥራ ዕድል መፍጠሩ ተገልጿል፡፡

በቀጣይም ማስፋፊያ በማድረግ ተጨማሪ የሥራ ዕድል እንደሚፈጥር መገለጹን የክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ መረጃ አመላክቷል፡፡