አዲስ አበባ፣ ግንቦት 5፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በደቡብ አፍሪካ የሕንጻ መደርመስ አደጋ ከደረሰ ከአምስት ቀናት ቆይታ በኋላ ሠራተኞች በሕይወት መገኘታቸው ተሰምቷል፡፡
በደቡብ አፍሪካ ጆርጅ ከተማ ከአምስት ቀናት በፊት በግንባታ ላይ የነበረ ግዙፍ ሕንጻ የመደርመስ አደጋ ደርሶበት እንደነበር ይታወሳል፡፡፡
ይህን ተከትሎም በወቅቱ በሥፍራው ነበሩ ከተበሉ 75 ሠራተኞች ቁጥሩ ጨምሮ 81 መድረሳቸው ተገልጿል፡፡
በተከሰተው አደጋ እስካሁን የ20 ሰዎች ሕይወት ያለፈ ሲሆን ፥ 32 ሠራተኞች ደግሞ አለመገኘታቸውን አርቲ ዘግቧል፡፡
በአንጻሩ ከአምስት ቀናት የሕንጻ መደርመስ አደጋ ቆይታ በኋላ የተገኙትን ሠራተኞች ጨምሮ 29 ሰዎች በሕይወት መገኘታቸው ብዙዎችን አስገርሟል፡፡
ከ100 የሚበልጡ የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች በአነፍናፊ ውሾች ታግዘው እና ትላልቅ ክሬኖች እና ከባድ የህንጻ መሳሪያዎችን በመጠቀም የነፍስ አድን ሥራው መቀጠሉም ተነግሯል፡፡