የሀገር ውስጥ ዜና

ከቢግ ዊን ፊላንትሮፒ ጋር በአዳዲስ ዘርፎች በትብብር ለመስራት ተስማምተናል – ም/ጠ/ሚ ተመስገን ጥሩነህ

By Amele Demsew

May 13, 2024

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 5፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ከቢግ ዊን ፊላንትሮፒ ጋር በጀመርናቸውና በሌሎች አዳዲስ ዘርፎች በትብብር ለመስራት ተስማምተናል ሲሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ገለጹ።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት፤ ዛሬ ከቢግ ዊን ፊላንትሮፒ መሥራች እና ፕሬዚዳንት ጄሚ ኩፐር እና ቡድናቸው ጋር መወያየታቸውን አመልክተዋል።

ድርጅቱ በኢትዮጵያ በግብርና፣ በትምህርት፣ በስራ ዕድል ፈጠራ እና ድህነት ቅነሳ ዘርፎች አበረታች ስራዎች መስራቱን ገልጸዋል።

ከቢግ ዊን ጋር በሰቆጣ ቃል ኪዳን አተገባበር እና በትብብር በሚሠሩ በሌሎች የልማት ሥራዎች ዙሪያ ምክክር መደረጉን የጠቀሱት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ይህን የትብብር ምዕራፍ ወደ ተሻለ ደረጃ ለማድረስ በጀመርናቸው እና በሌሎች አዳዲስ ዘርፎች በትብብር ለመስራት ተስማምተናል ብለዋል።