Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ሩሲያ ከዩክሬን የተሠነዘሩ የሚሳኤልና የድሮን ጥቃቶችን ማክሸፏን ገለጸች

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 5፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ሌሊቱን ዩክሬን ያስወነጨፈቻቸውን 16 ሚሳኤሎች ጨምሮ 31 ሰው አልባ አውሮፕላኖችን መትቶ መጣሉን የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

እንደ ሚኒስቴሩ ገለጻ÷ 12 ሚሳኤሎች በቤልጎሮድ ድንበር አካባቢ፣ 4 ሚሳኤሎች እና 7 ሰው አልባ አውሮፕላኖች በክሬሚያ፣ 8 ሰው አልባ አውሮፕላኖች በኩርስክ አካባቢ እንዲሁም 4 ሰው አልባ አውሮፕላኖች በሊፕትስክ ግዛት ተመትተው ወድቀዋል፡፡

በተጨማሪም አንድ ሰው አልባ አውሮፕላን በኩርስክ አካባቢ በሚገኝ የኤሌክትሪክ ማከፋፈያ ጣቢያ ላይ መውደቁን ተከትሎ የእሳት አደጋ መከሰቱን የሩሲያ ደቡባዊ ግዛት አሥተዳዳሪ ኢጎር አርታሞኖቭ ተናግረዋል፡፡

በሌላ በኩል በትናንትናው ዕለት ቤልጎሮድ ውስጥ በሩሲያ ጦር የተመታ ሚሳኤል ስብርባሪ አፓርታማ ላይ ወድቆ የ15 ሰዎች ሕይወት ማለፉን ሩሲያ ማሳወቋን ኤዥያ ዋን ዘግቧል፡፡

Exit mobile version