Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ሆራ ትሬዲንግ #ጽዱኢትዮጵያ ንቅናቄን ተቀላቀለ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 5፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ሆራ ትሬዲንግ ለ #ጽዱኢትዮጵያ 2 ሚሊየን ብር በማበርከት ንቅናቄውን መቀላቀሉን አስታውቋል።

የሕዝብ መፀዳጃ ቤቶችን በመገንባት ክብርን ጠብቆ የመፀዳዳት ባህልን ለማዳበር በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ባሳለፍነው ሚያዝያ ወር ይፋ የሆነውን የ“ጽዱ ጎዳና – ኑሮ በጤና” ንቅናቄ በርካቶች በመቀላቀል ድጋፍ እያደረጉ ይገኛል።

በትናንትናው ዕለትም በመላው ዓለም ከሚገኙ ኢትዮጵያውያን በአንድ ጀምበር ከ154 ሚሊየን ብር በላይ መሰብሰቡ ይታወሳል፡፡

Exit mobile version