Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የሕብረተሰቡን ጥያቄዎች የሚፈቱ ተግባራት ተከናውነዋል – አቶ አሻድሊ ሃሰን

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 4፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ባለፉት ዘጠኝ ወራት የሕብረተሰቡን ጥያቄዎች የሚመልሱ ተግባራት መከናወናቸውን የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አሻድሊ ሃሰን ገለጹ፡፡

የክልሉን ሠላም ለማጽናት በትኩረት መሠራቱን የገለጹት አቶ አሻድሊ÷ በመልሶ ማቋቋም ረገድም በክልሉ ከቀያቸው ከተፈናቀሉት መካከል አብዛኞቹን ወደ መደበኛ ኑሯቸው መመለስ ተችሏል ብለዋል፡፡

ሕብረተሰቡ የሚያነሳቸው የልማት ጥያቄዎችን ጨምሮ ባለፉት ዓመታት በተለያዩ ምክንያቶች ያልተከናወኑ በርካታ ተግባራት መኖራቸውንም ለኢዜአ ተናግረዋል፡፡

ተቋርጠው የቆዩ ትላልቅ የልማት ፕሮጀክቶች ግንባታቸው እንዲቀጥልና ለፍጻሜ እንዲቃረቡ የተደረገበት ሁኔታ መኖሩንም አስረድተዋል፡፡

እንዲሁም በሕዝቡ የተነሱ ከመንገድ፣ ውኃ፣ ማኅበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ተቋማት ጋር የተያያዙ ተግባራትን ለመመለስ ከፍተኛ ርብርብ መደረጉን አንስተዋል፡፡

Exit mobile version