አዲስ አበባ፣ ግንቦት 4፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ሁሉም ዜጋ ጽዱ ከተማና ከባቢ ለመፍጠር የተጀመረውን ንቅናቄ በመቀላቀል ዐሻራውን እንዲያር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ጥሪ አቀረቡ፡፡
ለጽዱ ኢትዮጵያ በአንድ ጀምበር 50 ሚሊየን ብር የማሰባሰብ የዲጂታል ቴሌቶን በመካሄድ ላይ ይገኛል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ዲጂታል ቴሌቶኑን አስመልክተው ባስተላለፉት መልዕክት ቴሌቶኑ ጽዱ ከተማና ከባቢ መፍጠርን ያለመ መሆኑን አስገንዝበው÷ የከተማ ገጽታን ከመቀየር ባሻገር የዜጎችን ጤና ለመጠበቅ ሚናው የጎላ መሆኑን አስረድተዋል፡፡
በመሆኑም ሁሉም ዜጋ ጽዱ ከተማና ከባቢ ለመፍጠር የተጀመረውን ንቅናቄ በመቀላቀል ዐሻራውን እንዲያሳርፍም ጠይቀዋል፡፡