Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እያንዳንዱ ዜጋ ለጽዱ ኢትዮጵያ ዲጂታል ቴሌቶን በሚያዋጣው 3 ብር ላይ የራሱን አንድ ብር ለመጨመር ቃል ገባ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 4፣2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እያንዳንዱ ዜጋ ለጽዱ ኢትዮጵያ ዲጂታል ቴሌቶን በሚያዋጣው 3 ብር ላይ የራሱን አንድ ብር ለመጨመር ቃል ገብቷል፡፡

በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ይፋ የተደረገው የ“ጽዱ ጎዳና – ኑሮ በጤና” ንቅናቄ በርካቶች በመቀላቀል ድጋፍ እያደረጉ ይገኛሉ።

በንቅናቄው በአንድ ጀምበር 50 ሚሊየን ብር ለማሰባሰብ ውጥን ተይዟል፡፡

በንቅናቄው በሀገር ውስጥና በውጭ የሚኖሩ ዜጎች፣ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች፣ ተቋማትና ሌሎችም አካላት ተሳትፈዋል።

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፕሬዚዳንት አቤ ሳኖ፤ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እያንዳንዱ ዜጋ ለጽዱ ኢትዮጵያ ዲጂታል ቴሌቶን በሚያዋጣው 3 ብር ላይ የራሱን አንድ ብር እንደሚጨምር አስታውቀዋል፡፡

ህብረተሰቡም ለንቅናቄው በተከፈተው ሂሳብ ቁጥር አማካኝነት ገንዘብ ገቢ በማድረግ በስፋት እየተሳተፈ ስለመሆኑም ተናግረዋል፡፡

በዚህም መሰረት በንግድ ባንክ በተከፈተው ሂሳብ ቁጥር 1000623230248፣ በብሔራዊ ባንክ የዶላር አካውንት 0101211300016 እና በስዊፍት ኮድ NBETETAA የ“ጽዱ ጎዳና – ኑሮ በጤና” ንቅናቄ እንዲቀላቀሉ ጥሪ ተደርጓል።

Exit mobile version