አዲስ አበባ፣ ግንቦት 2፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ማኔጅመንት የ3 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር ድጋፍን ጨምሮ የ”ፅዱ ኢትዮጵያ” ንቅናቄን የድጋፍ ማዕቀፍ አጽድቋል።
የዩኒቨርሲቲው ኤክስኪዩቲቭ ማኔጅመንት ባደረገው ስብሰባ የ”ፅዱ ኢትዮጵያ” ንቅናቄን በተመለከተ የተለያዩ ጉዳዮች ወስኗል፡፡
በንቅናቄው የተጀመረው የሃብት ማሰባሰብ ዘመቻን በተመለከተ ከዩኒቨርሲቲው የውስጥ ገቢ 3 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር እንዲተላለፍ ውሳኔ አሳልፏል።
ፕሮጀክቱ ወደ ስራ ሲገባ ከዩኒቨርሲቲው የጤና፣ የምህንድስና እና የከተማ ፕላን ሙያዊ ድጋፍ የሚሰጡ ሙያተኞችም እንዲቀርብ መወሰኑን ከዩኒቨርሲቲው ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
በተመሳሳይ በአዲሱ የራስገዝ ስትራቴጂክ ፕላን መሰረት መላው ግቢዎችንና የዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ አካባቢውን አረንጓዴና ፅዱ ለማድረግ እንዲረባረብና ይህንንም ኮሌጆችና የዩኒቨርሲቲው የማዕከል አመራር እንዲያስፈፅሙ ወስኗል።