አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 5 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የስፔን ላ ሊጋ ትናንት ምሽት በተደረገ አንድ ጨዋታ ዳግም ወደ ውድድር ተመልሷል።
ላ ሊጋው ትናንት ምሽት ሲጀመር ሲቪያ እና ሪያል ቤቲስን አገናኝቷል።
ከሶስት ወራት በኋላ ዳግም የተጀመረውን ላ ሊጋ ሲቪያ 2 ለ 0 ሲያሸንፍ፥ ኦካምፖስ እና ሬጌስ የድል ጎሎቹን አስቆጥረዋል።
በዝግ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ ከጨዋታው አስቀድሞ የተወሰኑ የሲቪያ ደጋፊዎች በስታዲየሙ ዙሪያ ተሰባስበው ታይተዋል።
ይህ ደግሞ በኮሮና ቫይረስ ሳቢያ የተላለፈውን መመሪያ የጣሰ ነው በሚል አንዳንዶች ዳግም በተጀመረው ውድድር ዙሪያ ከወዲሁ ስጋታቸውን እየገለጹ ነው።
ጨዋታው በኮሮና ቫይረስ ሳቢያ ህይዎታቸውን ላጡ ሰዎች የህሊና ፀሎት በማድረግ ተጀምሯል።
ላ ሊጋው ዛሬም ሲቀጥል ግራናዳ ከጌታፌ እንዲሁም ቫሌንሲያ ከሌቫንቴ ይጫወታሉ።
ነገ ደግሞ ባርሴሎና ከሜዳው ውጭ ከማዮርካ ሲጫወት ሪያል ማድሪድ ደግሞ ኤባርን ከነገ በስቲያ ያስተናግዳል።
ቀደም ብሎ የጀርመን ቡንደስ ሊጋ የተጀመረ ሲሆን፥ የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ደግሞ በቀጣዩ ሳምንት አጋማሽ በሚደረጉ ሁለት ጨዋታዎች ይጀመራል።