Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ፕሬዚዳንት ፑቱን የሩሲያ ወታደራዊ ሀይል የሀገሪቱን ሉዓላዊነት ለማስጠበቅ በተጠንቀቅ ላይ መሆኑን ገለጹ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 1፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የሩሲያ ወታደራዊ ሀይል ከጠላት ሊሰነዘር የሚችልን ጥቃት ለመመከት በተጠንቀቅ ላይ እንደሚገኝ ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን ገለፁ፡፡

ሩሲያ በናዚ ላይ ድል የተቀዳጀችበትን 79ኛ ዓመት በተለያዩ ወታደራዊ ትርኢቶች በሞስኮ ከተማ አክብራለች፡፡

በበዓሉ ላይ ንግግር ያደረጉት ፕሬዚዳንት ፑቲን÷ ሩሲያ በዓለም ላይ ግጭት እንዳይከሰት የምትችለውን ሁሉ ታደርጋለች፣ ነገር ግን የማንኛውንም ሀይል ዛቻ እና ማስፈራሪያ አትታገስም ብለዋል፡፡

ምዕራባውያን ከሁለተኛው ዓለም ጦርነት ትምህርት እንዳልወሰዱ በመጥቀስ÷ ፀብ አጫሪነታቸውን የማያቆሙ ከሆነ ሩሲያ በሌኒንግራድ ከተማ ያደረገችውን የሁለተኛው የዓለም ጦርነት ድል አሁንም ትደግመዋለች ብለዋል፡፡

የድል በዓሉ የሩሲያ ወታደሮች በተለያዩ አውደ ወጊያዎች ዋጋ እየከፈሉ ባሉበት መሆኑን ጠቅሰው፤ የሩሲያ ወታደራዊ ሀይል ላሳየው ጽናትና መስዋዕትነት ከፍተኛ አድናቆት እና ክብር ሰጥተዋል፡፡

ሩሲያ በታሪኳ አስቸጋሪ ምዕራፎችን እያለፈች ነው ያሉት ፕሬዚዳንቱ÷ ይህን አስቸጋሪ ጊዜ ለማለፍ የሩሲያ እጣ ፋንታ በእያንዳንዱ ሩሲያውያን እጅ ላይ ወድቋል ብለዋል፡፡

በዛሬው እለት በፈረንጆቹ ግንቦት 9 ቀን 1945 በቀድሞዋ ሌኒንግራድ በአሁኗ ቅዱስ ፒተርስበርግ ከተማ በተደረገው ውጊያ ሩሲያ ናዚን ድል ማድረጓን አርቲ ዘግቧል፡፡

Exit mobile version