Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ከቤንዚን ውጪ የነዳጅ ምርቶች ዋጋ ባለበት ይቀጥላል

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 30፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ከግንቦት 1 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ ከቤንዚን ውጪ የነዳጅ ምርቶች ዋጋ ባለበት እንደሚቀጥል የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስታወቀ።

በዓለም ገበያ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየታየ የመጣውን የነዳጅ ዋጋ ጭማሪ መነሻ በማድረግ በቤንዚን የችርቻሮ መሸጫ ላይ ብቻ መጠነኛ ማሻሻያ መደረጉን ሚኒስቴሩ አመልክቷል።

በመሆኑም ከግንቦት 1 ቀን 2016 ከምሽቱ 6፡00 ሰዓት ጀምሮ በሥራ ላይ ያለው የነጭ ናፍጣ፣ የኬሮሲን፣ የአይሮፕላን ነዳጅ፣ የቀላል ጥቁር ናፍጣ እና የከባድ ጥቁር ናፍጣ የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ባለበት ይቀጥላል።

በዚህም መሰረት:-
ቤንዚን ……………………………………… ብር 78.67 በሊትር
ነጭ ናፍጣ………………………………… ብር 79.75 በሊትር
ኬሮሲን …………………………………… ብር 79.75 በሊትር
የአውሮፕላን ነዳጅ ………………… ብር 70.83 በሊትር
ቀላል ጥቁር ናፍጣ…………………… ብር 62.36 በሊትር
ከባድ ጥቁር ናፍጣ…………………. ብር 61.16 በሊትር ሆኗል።

Exit mobile version