Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ኢትዮጵያ እና የኮንጎ ሪፐብሊክ የአየር ትራንስፖርትን ለማሳለጥ ያለመ ስምምነት ተፈራረሙ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 30፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባላስልጣን እና የኮንጎ ሪፐብሊክ የአየር ትራንስፖርት የመግባቢያ ስምምነት ተፈራርመዋል፡፡

የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባላስልጣን ዋና ዳይሬክተር ጌታቸው መንግሥቴ በፊርማ ሥነ-ሥርዓቱ ላይ እንዳሉት÷ ስምምነቱ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ኮንጎ ሪፐብሊክ የሚያደርገውን በረራ የተሳካ በማድረግ በኩል ትልቅ አስተዋፅኦ አለው፡፡

እንዲሁም ወደ ጎንጎ ሪፐብሊክ የሚደረጉ በረራዎን ቁጥር ለማሳደግ እንደሚያግዝ ነው ያስገነዘቡት፡፡

በሀገራቱ መካከል ከሚኖረው የአየር ትራንስፖርት ምልልስ በተጨማሪ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከኮንጎ ሪፐብሊክ ጋር ደርቦ ወደ ሌላ ሀገር መብረር የሚያስችለውን የትራፊክ መብትም ስምምነቱ እንደሚያጠቃልል ጠቁመዋል፡፡

ስምምነቱ የአየር ትራንስፖርት ፍላጎቱን ለማሟላት እና ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ትልቅ ገበያ የሚፈጥር መሆኑንም አንስተዋል።

Exit mobile version