ቢዝነስ

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል 4 ነጥብ 1 ቢሊየን ብር ገቢ ተሰበሰበ

By Mikias Ayele

May 06, 2024

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 28፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ገቢዎች ቢሮ ባለፉት ዘጠኝ ወራት ከ4 ነጥብ 1 ቢሊየን ብር በላይ ገቢ መሰብሰቡን አስታወቀ፡፡

የቢሮው ሃላፊ ወ/ሮ ህይወት አሰግድ ÷የገቢ አሰባሰቡን ውጤታማ ለማድረግ አማራጮችን የማስፋትና የህግ ማዕቀፎችን ማሻሻል ላይ ሰፊ ሥራ መሰራቱን ተናግረዋል።

በዚህም ባለፉት 9 ወራት ከመደበኛና ማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎቶች 4 አራት ነጥብ 1 ቢሊየን ብር በመሰብሰብ የዕቅዱን 86 በመቶ ማሳካት መቻሉን ተናግረዋል።

ገቢው ካለፉው ተመሳሳይ ወቅት አንጻር የተሻለ መሆኑን ጠቁመው÷ የባለሙያዎች ቁርጠኝነት ማሳደግ፣ በደረሰኝ አጠቃቀምና የግብር ከፋዮን ግንዛቤ የማስፋት ስራ መሠራቱን ተናግረዋል።

የገቢ አሰባሰብ ሥርዓቱን በማዘመን በዘርፉ የሚስተዋለውን የገቢ ስወራ፣ ሌብነትን በመከላከል የክልሉን ገቢ አቅም ለማሳደግ በትኩረት እንደሚሰራም አንስተዋል።