አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 28፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በምሥራቅ ራፋህ የተጠለሉ ጋዛውያን አካባቢውን ለቀው እንዲወጡ የእስራኤል ጦር አሳሰበ፡፡
በአካባቢው ውጥረት የነገሰው በጋዛ የተኩስ አቁም ስምምነትን ለማስፈን እና ታጋቾችን ለማስፈታት ያለሙ ንግግሮች ሊቋረጡ መሆናቸውን ተከትሎ ነው ተብሏል፡፡
በሌላ በኩል ወደ ጋዛ ሰብዓዊ ዕርዳታ ለማቅረብ በሚያገለግለው በኬረም ሻሎም ማቋረጫ አቅራቢያ ሃማስ 10 ሮኬቶችን ማስወንጨፉንና በጥቃቱም ሦስት ወታደሮቿ መገደላቸውን እስራኤል አስታውቃለች፡፡
ለጥቃቱ የሃማስ ታጣቂ ክንፍ ኃላፊነቱን መውሰዱን እና ዒላማውም በአቅራቢያው በሚገኝ የእስራኤል ጦር ሰፈር ላይ ማነጣጠሩን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡
ጥቃቱን ተከትሎም የእስራኤል ጦር የኬረም ሻሎም ማቋረጫን ሌሊቱን መዝጋቱ እና በደቡባዊ የጋዛ ከተማ ራፋህ በፈጸመው ጥቃት በትንሹ የ12 ሰዎች ሕይወት ማለፉ ተገልጿል፡፡