Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በአቶ ሽመልስ አብዲሳ የተመራ ልዑክ በጅቡቲ ጉብኝት እያደረገ ነው

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 1፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በኦሮሚያ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ የተመራ የመንግስት ልዑካን ቡድን በጅቡቲ ጉብኝት እያደረገ ነው።

ልዑኩ ጅቡቲ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርስም በጅቡቲ የኢትዮጵያ አምባሳደር አብዱላዚዝ መሃመድ አቀባበል ተደርጎለታል።

በቆይታውም ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊ እና ፖለቲካዊ ግንኙነቶችን ማጠናከር በሚቻልባቸው ጉዳዮች ዙሪያ ከሀገሪቱ ባለስልጣናት ጋር በመገናኘት እንደሚመክር ይጠበቃል።

Exit mobile version