አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 25፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 23ኛ ሳምንት ኢትዮጵያ መድን ሀምበሪቾን 2 ለ 0 በሆነ ውጤት አሸነፈ።
በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም 9:00 ሰዓት ላይ በተካሄደው ጨዋታ አቡበከር ሳኒ በ68ኛው እና በ75ኛው ደቂቃ ባስቆጠራቸው ጎሎች ኢትዮጵያ መድን ተጋጣሚውን ሀምበሪቾን አሸንፎ ሶስት ነጥብ ይዞ ወጥቷል።
በተመሳሳይ በዛሬው የጨዋታ መርሃ ግብር የሊጉ መሪ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክና ኢትዮጵያ ቡና 12 ሰዓት ላይ ባደረጉት ጨዋታ 2 ለ 2 በሆነ አቻ ውጤት ተለያይተዋል።
ሲሞን ፒተር በ5ኛው እና በ43ኛው ደቂቃ ባስቆጠራቸው 2 ጎሎች ሲመራ ቢቆይም፤ አማኑኤል ዮሐንስ 84ኛው ደቂቃ እንዲሁም ፈቱዲን ጀማል በ90+3′ በራስ ላይ ባስቆጠሯቸው ጎሎች ኢትዮጵያ ቡና ነጥብ ተጋርቶ ወጥቷል።