Fana: At a Speed of Life!

በ300 ሚሊየን ብር ለሚገነባ የመድሃኒት ማከማቻ መጋዘን የመሰረተ ድንጋይ ተቀመጠ

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 23፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በጅግጅጋ ከተማ በ300 ሚሊየን ብር ወጪ የመድኃኒት ግብዓት ማከማቻ መጋዘን እና የአስተዳደር ህንጻ ግንባታ የመሰረተ ድንጋይ ተቀመጠ፡፡

የመሰረት ድንጋዩን  የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳደር ሙስጠፌ መሃመድ እና የጤና ሚኒስትር  ዶ/ር መቅደስ ዳባ አስቀምጠዋል፡፡

አቶ ሙስጠፌ  በዚህ ወቅት እንዳሉት÷ ፕሮጀክቱ በክልሉ የጤና አገልግሎት ጥራት እና ተደራሽነትን ለማሳደግ ያስችላል፡፡

ግንባታው በታቀደለት ጊዜ እንዲጠናቀቅ የክልሉ መንግስት አስፈላጊውን እገዛ  እንደሚያደርግ ነው ያረጋገጡት፡፡

ዶ/ር  መቅደስ ዳባ  በበኩላቸው ÷  እንደ አዲስ የተከለሰው የጤና ፖሊሲ በዋናነት የህብረተሰቡን ጤና ለመጠበቅ  የበሽታ መከላከል ላይ ትኩረቱን እንደሚያደርግ ገልፀዋል፡፡

ለፖሊሲው ውጤታማነትም  ወሳኝ ከሆኑ ጉዳዮች መካከል አንዱ ያልተቆራረጠ የመድኃኒትና የሕክምና መገልገያ መሳሪያዎች አቅርቦት  መሆኑን  አንስተዋል፡፡

ለዚህም በጅግጅጋ የሚገነባው የመጋዝን  እና ህንፃ ግንባታ ጉልህ ሚና እንደሚጫዎት ተናግረዋል፡፡

ግንባታው በ300 ሚሊየን ብር ወጪ በኢትዮጵያ መድኃኒትና አቅራቢ አገልግሎትና በጤና ሚኒስቴር በትብብር የሚገነባ መሆኑን የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.