Fana: At a Speed of Life!

በቻይና በአውራ ጎዳና መደርመስ የ19 ሰዎች ህይወት አለፈ

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 23፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በቻይና ለቀናት የጣለውን ከባድ ዝናብ ተከትሎ በጉዋንግዶንግ ግዛት በአውራ ጎዳና ላይ በደረሰ የመደርመስ አደጋ የ19 ሰዎች ህይወት ማለፉ ተገልጿል፡፡

በአደጋው ጉዳት የደረሰባቸው ሌሎች 30 ሰዎች ወደ ሆስፒታል መወሰዳቸው የተገለጸ ሲሆን ለህይወታቸው አስጊ ነገር እንደሌለም ተመላክቷል፡፡

የግዛቱ አስተዳደር 500 የሚሆኑ የድንገተኛ አደጋ ምላሽ ሰጪ ሰራተኞችን ማሰማራቱም ተጠቁሟል፡፡

በአደጋው ወቅት የተነሱ ምስሎች ከመንገዱ ስር የእሳት ነበልባል እና ጥቁር ጪስ ማሳየታቸውም ተነግሯል፡፡

በሌላ በመንግስት ቴሌቪዥን የተቀረፀ ተንቀሳቃሽ ምስል ደግሞ በከፊል በጭቃ የተሸፈኑ የተቃጠሉ መኪኖች እና ጭስ አሳይቷል።

የአካባቢው ባስልጣናትም የአደጋውን ትክክለኛ መንስኤ አለመግለፃቸውን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

በቻይና በሕዝብ ብዛት ቀዳሚ የሆነችው ጉዋንግዶንግ ባለፈው ሳምንት በከባድ ጎርፍ መመታቷና በአደጋውም የአራት ሰዎች ህይወት ማለፉ ይታወቃል፡፡

በተጨማሪም 110 ሺህ ሰዎች መፈናቀላቸው፣ ብዙ ቤቶች መውደማቸው፣ ት/ቤቶች መዘጋታቸው እና በረራዎችም እንዲዘገዩና እንዲሰረዙ መደረጋቸው በዚህም 19 ነጥብ 4 ሚሊየን ዶላር ኪሳራ መድረሱ ይታወሳል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.