Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ከበዓል ጋር ተያይዞ የኑሮ ውድነትን ለመከላከል በተዘጋጀ ዕቅድ ላይ ውይይት ተደረገ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 22፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የ2016 ዓ.ም የትንሣዔ በዓልን ምክያት በማድረግ ሰው ሠራሽ የኑሮ ውድነት እንዳይባባስ ለመከላከል በተዘጋጀ የማስፈፀሚያ ዕቅድ ላይ ግብረ-ኃይሉ መከረ፡፡

ከበዓሉ ጋር በተያያዘ ጤናማ ግብይት እንዲኖርም ግብረ-ኃይሉ ሥድስት አቅጣጫዎችን አስቀምጧል፡፡

በዚሁ መሠረት÷ በበዓሉ ላይ ከተቀመጠው የዋጋ ተመን ውጭ ሽያጭ እንዳይኖር፣ ከገበያ ማዕከል ውጪ የቁም እንስሳት ግብይት እንዳይፈጸም፣ ሕገ-ወጥ የእንስሳት ዕርድ እንዳይኖር ክትትል ማድረግ እና በጎዳና ላይ ንግድም ክትትል እንዲደረግ አቅጣጫ ተቀምጧል፡፡

እንዲሁም በሁሉም የከተማዋ መግቢያ በሮች የሚገቡ ምርቶች ላይ የዋጋ ጭማሬ እንዳይከሰት ከሸገር አጎራባች ከተሞች ጋር በቅንጅት ለመስራትና የገበያ ማዕከላት ላይ ውዝግብ በመፍጠር ዋጋ የሚጨምሩ ነጋዴዎች ላይ አሥተዳደራዊና ሕጋዊ ርምጃ ለመውሰድ አቅጣጫ ተቀምጧል።

በተጨማሪም ለማኅበረሰቡ በዝቅተኛ ዋጋ በመሸጥ ገበያ እንዲረጋጋ የታሰበው የእሁድ ገበያ ላይም ዋጋ እንዳይጨምሩ ክትትልና ቁጥጥር እንዲደረግ ግብረ-ኃይሉ አቅጣጫ አስቀምጧል፡፡

በሌላ በኩል ሐሰተኛ የብር ኖቶች ግብይት ላይ ሊውሉ ስለሚችሉ ግብረ-ኃይሉ የክትትልና ቁጥጥር ሥራውን እንደሚያጠናክር አስታውቋል፡፡

Exit mobile version