አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 21፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የተመራ ልዑክ በዓለም አቀፉ የልማት ማኅበር (አይ ዲ ኤ) 21ኛ የማሟያ ጉባዔ ላይ ለመገኘት ኬንያ ናይሮቢ ገባ፡፡
ጉባዔው የማኅበሩ ደጋፊዎች እና ተባባሪ አካላት በአፍሪካ የልማት የገንዘብ ድጋፍ ቀዳሚ የትኩረት መስኮችን ለማመላከት እና አፅንዖት ለመስጠት ያለመ መሆኑን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት መረጃ አመላክቷል፡፡
በተጨማሪም የገንዘብ ድጋፍ አቅራቢዎች በ21ኛው የማኅበሩ ዘመን ድጋፋቸውን ለመጨመር በፅኑ እንዲያጤኑ የማሳሰብ ዓላማ እንዳለውም ነው የተገለጸው፡፡
ይህ ድጋፍ የአፍሪካን የልማት ተግዳሮቶች እና መልካም እድሎች በተገቢው መንገድ ለማስተናገድ እጅግ አስፈላጊ መሆኑም ተጠቅሷል፡፡