አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 21፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የሀገር ውስጥ አምራቾችን ለማበረታታ እና ለሀገር ውስጥ ምርቶች ቅድሚያ ለመስጠት በተቀመጠው አቅጣጫ መሰረት በአውቶሞቲቭ ዘርፉ የሳፋሪ ተሽከርካሪዎችን ለማምረት በትኩረት እየተሠራ መሆኑ ተገለጸ፡፡
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የማዕድንና ኢንዱስትሪ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አመራሮችና አባላት የሳፋሪ ተሽከርካሪ የምርት ሂደት ያለበትን ደረጃ በቢሾፍቱ አውቶሞቲቭ ማምረቻ ኢንዱስትሪ ጎብኝተዋል፡፡
በዚሁ ወቅትም የሀገር ውስጥ አምራቾችን ለማበረታታ እና ለሀገር ውስጥ ምርቶች ቅድሚያ ለመስጠት በተቀመጠው አቅጣጫ መሰረት በአውቶሞቲቭ ዘርፉ የሳፋሪ ተሽከርካሪዎችን ለማምረት ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ መሆኑ ተገልጿል።
በተለይም የቴክኖሎጂ ሽግግርን በማስፋት ለቱሪዝም ዘርፉ ምቹ ሁኔታዎችን ለመፍጠር፣ ለዜጎች ዘላቂ የሥራ ዕድል ለመፍጠር የሳፋሪ ተሽከርካሪዎች ሚና የጎላ መሆኑን የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት መረጃ አመላክቷል፡፡