አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 19፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) አውደ ርዕይው በተለያዩ መርሐ ግብሮች ለሦስት ሳምንታት ሲካሄድ ቆይቶ ዛሬ የማጠናቀቂያ መርሐ ግብሩ ተካሂዷል፡፡
በአውደ ርዕይው ስራዎቻቸውን ለውድድር ያቀረቡ እና ከአንድ እስከ ሦስት ለወጡ ስታርት አፖችን እውቅና እና ሽልማት ተሰጥቷል፡፡
በውድድሩ ከአንድ እስከ አሥር ለወጡት ተወዳዳሪዎችም ስራ የሚጀምሩበት መነሻ ካፒታል ድጋፍ ይደረግላቸዋል ተብሏል፡፡
በመርሐ ግብሩ የስራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪያት ካሚል እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።
በአውደ ርዕይው የተሳተፉ የስታርት አፕ ስራዎችን ከ16 ሺህ በላይ ሰዎች ጎብኝተውታል።
በይስማው አደራው