አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 18፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የዓለም የአዕምሮሯዊ ንብረት ቀን በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ24ኛ ጊዜ በኢትዮጵያ ደግሞ ለ22 ኛጊዜ በሳይንስ ሙዚየም እየተከበረ ይገኛል፡፡
የዘንድሮ የአዕምሯዊ ቀን “የአዕምሯዊ ንብረት ለዘላቂ ልማት፤ መጪው ጊዜያችንን በፈጠራና ኢኖቬሽን እንገንባ” በሚል መሪ ሀሳብ እየተከበረ ነው።
የኢትዮጵያ አዕምሯዊ ንብረት ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ወልዱ ይመስል፤ ቀኑን ስናከብር የፈጠራ ውጤቶች እንዲከበሩ ሁሉን አሳታፊ ያደረገ ስራ መስራት እንደሚያስፈልግም ሊታመን ይገባል ብለዋል።
ይህን ለማስጠበቅ ህጎችን ማስተካከል እንደሚገባና በዚህም መንግስት ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑ ተናግረዋል፡፡
ባለስልጣኑ የፓተንት፣ የመገልገያ ሞዴል፣ ኢንዱስትሪያዊ ንድፍ፣ የንግድ ምልክት፣ እንዲሁም የስነፅሁፍ እና የጥበብ ስራዎች የቅጅ መብት በቂ የህግ ጥበቃ የሚያስገኙበትን ምቹ መደላድል መፍጠርን ዋነኛ ዓላማው በማድረግ እየሰራ መሆኑንም አመላክተዋል።
በስ ነስርዓቱ ላይ የተገኙት የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ የሽሩን ዮሃንስ (ዶ/ር) ለስታርት አፕ መንግስት የሰጠው ትኩረት ለአዕምሯዊ ንብረት የተጠውን ትኩረት ያሳያል ብለዋል።
ይህም በ2030 የዘላቂ ልማት አጀንዳን ለህዝብ ሰላም እና ብልፅግና ወሳኝ የሆኑ 17 የልማት ግቦችን በግልፅ ያስቀመጠ ነው ተብሏል።
በፈቲያ አብደላ