አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 18፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ስዊድን ከ1 ነጥብ 2 ቢሊየን ብር በላይ (238 ሚሊየን የስዊዲን ክሮና) በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ላሉ ኢትዮጵያውያን የሚውል ድጋፍ ማስተላለፏ ተገልጿል፡፡
ስዊድን የምግብ፣ የውሃ፣ የመጠለያ፣ የጤና እንክብካቤ እና ጥበቃ የሚያስፈልጋቸውን ተጋላጭ ሰዎችን ለመደገፍ ቁርጠኛ መሆኗን አስታውቃለች፡፡
በዚህም በስትራቴጂካዊ የሰብአዊነት አጋሮቻችን በኩል ስዊድን በፈረንጆቹ 2024 ለ30 የሰብኣዊ ቀውስ ክስተቶች ምላሽ እንዲሆን 4 ነጥብ 3 ቢሊየን የስዊድን ክሮና አስተላልፌያለሁ ብላለች፡፡
ከዚህ ጋር ተያይዞ ተጠቃሚ ከሚሆኑት ውስጥ በኢትዮጵያ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ያሉ ዜጎች መሆናቸውም ተገልጿል፡፡
በዚህም ከ1 ነጥብ 2 ቢሊየን ብር በላይ (238 በላይ ክሮና) ድጋፍ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ላሉ ኢትዮጵያውያን እንዲሆን ማስተላለፏን በአዲስ አበባ ከሚገኘው የስዊድን ኤምባሲ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡