የኮምፒውተር ቫይረሶችን እንዴት መከላከል ይቻላል?
አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 17፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የኮምፒውተር ቫይረሶች የሚጠቀሙበት ኮምፒውተር ውስጥ በተለያዩ ምክንያቶች ሰርጎ በመግባት መጠነ ሰፊ ጉዳቶችን ሊያደርሱ ይችላሉ፡፡
ጉዳቱን ለመከላከል ምን ማድረግ ይገባል?
1.የጸረ-ቫይረስ ሶፍትዌር መጠቀም፡- ትክክለኛ የጸረ-ቫይረስ መተግበሪያን በመጫን ኮምፒውተርዎን ከቫይረሶች፣ ከስፓይዌሮች እና ከሌሎች ማልዌሮች መጠበቅና አዳዲስ ስጋቶችን ለመቋቋም በየጊዜው ማዘመን ያስፈልጋል።
2. ከማናውቃቸው ተጠቃሚዎች የሚላኩ ኢሜይሎችን አለመክፈት፡- አንዳንድ ወንጀለኞች ቫይረሶችን እና ማልዌሮችን ከኢሜይል መልእክት ጋር በማያያዝ ያሰራጫሉ። እንደዚህ ዓይነት መልእክቶች ስንከፍታቸው ቫይረሶች ወይም ማልዌሮች ኮምፒተርዎን በማጥቃት መረጃ ወይም ገንዘብ ይሰርቃሉ፡፡ በመሆኑም ከማናውቃቸው ተጠቃሚዎች የሚላኩ ኢሜይሎችን አለመክፈት ያስፈልጋል፡፡
3. የተጠረጠሩ ድር ገጾችን አለመክፈት፡- ሁሉም ድረ-ገጾች ጤናማ ስለማይሆኑ፣ የድረ-ገጽ ማሰሻችን ልንጎበኝ የፈለግነው ድህረ ገጽ ደህንነቱ የተጠበቀ እንዳልሆነ ወይም ድህረ ገጹ በኮምፒውተርዎ ላይ ፕሮግራም ለመጫን ወይም ለማስኬድ እንደሚሞክር ሊያሳውቅዎ ይችላል።
4. የበይነመረብ አሳሽ የደህንነት ቅንብሮችን ማጠናከር፡- ብዙውን ጊዜ ቫይረሶች፣ ማልዌር እና ስፓይዌር የሚመጡት በኢንተርኔት አማካኝነት ስለሆነ የበይነመረብ አሳሽዎን የደህንነት ቅንጅቶች ማጠናከር አስፈላጊ ነው፡፡
5. ስማርት ስክሪን ማጣሪያን (SmartScreen Filter) ማስተግበር፡- የማይክሮሶፍት ኤጅ (Microsoft Edge) የሚጠቀሙ ከሆነ መመሪያ ስለሚሰጥዎ የስማርትስክሪንን ማንቃት ይችላሉ። ይህም ደህንነታቸው ያልተጠበቁ ድረ-ገጾችን ለመጎብኘት ሲሞክሩ ማስጠንቀቂያ ይሰጥዎታል፡፡
6. ለዊንዶውስ ስማርት ስክሪን ማስጠንቀቂያ ትኩረት መስጠት፡- የዊንዶውስ ስማርት ስክሪን ከበራ የዊንዶውስ ስቶር መተግበሪያዎችን ሲጠቀሙ ለሚያገኟቸው ማሳወቂያዎች(notifications) ትኩረት መስጠት ይኖርብዎታል ።
7. ዊንዶውስን ወቅታዊ ማድረግ(update window)፡- ማይክሮሶፍት በየጊዜው ስህተቶች እና የደህንነት ክፍተቶች ላይ ማስተካከያ ያደረገባቸውን የደህንነት ዝመናዎች ይለቃል። ስለዚህ፣ ኮምፒውተርዎን ከጥቃት ለመጠበቅ፣ በየጊዜው ማዘመን (ወቅታዊ ማድረግ) ያስፈልጋል።
8. የፋየርዎል (Firewall) መተግበሪያን መጠቀም፡- የፋየርዎል መተግበሪያ ቫይረስ ከኮምፒውተርዎ ጋር ለመገናኘት ሲሞክር ሊያሳውቅዎ ይችላል። እንዲሁም ቫይረሶችን፣ ዎርሞችን እና አጥቂዎችን ኮምፒውተርዎን ሊጎዱ የሚችሉ መተግበሪያዎችን እንዳያዎርዱ ሊያግዝዎ ይችላል።
9. የተጠቃሚ መለያ መቆጣጠሪያን User Account Control (UAC) ማብራት/ማንቃት፡- የተጠቃሚ መለያ ቁጥጥር በዊንዶው ላይ መሰረታዊ የደህንነት አካል ነው። አንዳንድ ለውጦች በኮምፒውተርዎ ላይ ሲደረግ እና የአስተዳዳሪ ደረጃ ፈቃድ ሲፈልጉግ፣ የተጠቃሚ መለያ መቆጣጠሪያን ብቅ ይላል እና ለውጡን ላለመቀበል ወይም ለማጽደቅ ምርጫ ይሰጣል። ይህም ተግባር የማልዌር ተፅእኖን ሊቀንስ ይችላል።
10. የድር አሳሽ (Web browser) ታሪክን መከታተል እና ማጽዳት፡- ድረ-ገጾችን ለመጎብኘት ዌብ ማሰሻን ሲጠቀሙ የሚያቀርቡትን የግል መረጃዎች እንደስም፣ አድራሻ፣ አንዳንድ የይለፍ ቃሎች እና ሌሎችንም ሊይዙ ይችላሉ። የድር አሳሽዎ ይህን መረጃ እንዳያስታውስ ከመውጣትዎ በፊት መረጃዎን ማስወገድ አለብዎ።
11. የተሰረቀ ሶፍትዌር (Cracked Software) አለመጫን ፡- ብዙውን ጊዜ ለእውነተኛ ሶፍትዌሮች መክፈል ይኖርብዎታል፡፡ ሆኖም ግን የተሰረቀ ሶፍትዌር ነፃ በመሆኑ በምፒውተርዎ ላይ መጫን (ማውረድ) የለብዎም ምክንያቱም ኮምፒተርዎንን ከቫይረሶች ለመጠበቅ አያስችልዎትም፡፡
12. ስለሚያዎርዷቸው ፋይሎች ጥንቃቄ ማድረግ፡- ደህንነቱ ያልተጠበቀ እንደ ሙዚቃ፣ ፊልሞች፣ ሰነዶች፣ ወዘተ ያሉ ፋይሎችን ወደ ኮምፒውተርዎ የሚያዎርዱ ከሆነ በቫይረስ የተጠቁ ሊሆኑ ስለሚችሉ ጥንቃቄ ማድረግ ይኖርብዎታል ሲል የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ይመክራል።