Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

አሜሪካ ለዩክሬን የረጅም ርቀት ተምዘግዛጊ ሚሳኤሎችን መስጠቷ ተነገረ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 17፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) አሜሪካ ለዩክሬን የረጅም ርቀት ተምዘግዛጊ ባለስቲክ ሚሳኤሎችን መስጠቷ ተሰምቷል፡፡

ዩክሬን የረጅም ርቀት ተምዘግዛጊ ባለስቲክ ሚሳኤሎችን በሩሲያ ላይ ቢያንስ አንድ ጊዜ መጠቀም መጀመሯን የአሜሪካ ባለስልጣናት ማረጋገጣቸውም ነው የተገለጸው፡፡

መሳሪያዎቹ በመጋቢት ወር በአሜሪካ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን የፀደቀው የ300 ሚሊየን ዶላር የእርዳታ አካል ነው የተባለ ሲሆን፥ በዚህ ወር ዩክሬን መድረሳቸውም ተነግሯል፡፡

ባይደን በተጨማሪም አሁን ላይ ለዩክሬን የ61 ቢሊየን ዶላር እርዳታ መፈረማቸውም ነው የተገለጸው፡፡

ፕሬዚዳንቱ በዚህ ወቅት “አሜሪካ የበለጠ ደህንነቷ የተጠበቀ ይሆናል፣ የዓለም እንዲሁ” ብለዋል።

የዩክሬን ፕሬዚዳንት ቮላድሚር ዘለንስኪ “አሁን በክርክር እና በጥርጣሬ ያሳለፍነውን ግማሽ ዓመት ለማካካስ ሁሉንም ነገር እናደርጋለን” ሲሉም ምላሽ መስጠታቸውን የዘገበው ቢቢሲ ነው።

ዩክሬን አቪዲቪካ ከተማን ካጣች በኋላ በሚቀጥሉት ሳምንታት የሩሲያ ጥቃት እንደሚጠበቅም በቅርቡ ማስጠንቀቃቸው የሚታወስ ነው።

ሩሲያና ዩክሬን ጦርነት ከጀመሩ ወዲህ በሁለቱም በኩል በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች (በአብዛኛው ወታደሮች) ለህልፈት ተዳርገዋል፤ ሚሊየኖችም ከቀያቸው ተፈናቅለዋል፡፡

Exit mobile version