ቴክ

ኢትዮ ቴሌኮም በሀገር አቀፍ ደረጃ የብሄራዊ ዲጂታል መታወቂያ ምዝገባን አስጀመረ

By Mikias Ayele

April 24, 2024

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 16፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮ ቴሌኮም በሀገር አቀፍ ደረጃ የብሄራዊ ዲጂታል መታወቂያ ምዝገባን አስጀምሯል፡፡

በማስጀመሪያ ሥነ-ሥርዓቱ ላይ በወር በአማካይ 1 ሚሊየን ዜጎችን በመመዝገብ እስከ 2018 ዓ.ም ለ32 ሚሊየን ዜጎች አገልግሎቱን ለመስጠት መታቀዱ ተመላክቷል፡፡

የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈፃሚ ፍሬህይወት ታምሩ÷ ዲጂታል ኢትዮጵያን እውን ለማድረግ አስቻይ ከሆኑ ጉዳዮች አንዱ ተዓማኒነት ያለው የማንነት መለያ ዲጂታል መታወቂያ ነው ብለዋል።

ዲጂታል መታወቂያ አካታች ዲጂታል ኢኮኖሚን ለመገንባትና ዜጎች በኢኮኖሚው ዕኩል ተጠቃሚ እንዲሆኑ ዕድል ይፈጥራል ነው ያሉት፡፡

የብሔራዊ ዲጅታል መታወቂያ ምዝገባው አዲስ አበባን ጨምሮ በ29 ከተሞች ዛሬ በይፋ መጀመሩን አስታውቀዋል፡፡

በለይኩን አለም