የሀገር ውስጥ ዜና

በትራፊክ አደጋ የ4 ሰዎች ሕይወት አለፈ

By Feven Bishaw

April 23, 2024

 

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 15፣ 2016 (ኤፍቢ ሲ) በሰሜን ሸዋ ዞን ደብረ ሊባኖስ ወረዳ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የአራት ሰዎች ሕይወት አለፈ።

አደጋው የተከሰተው ከአዲስ አበባ ወደ ደብረ ሊባኖስ ገዳም ሲጓዝ የነበረ የቤት መኪና በተቃራኒ አቅጣጫ ሲጓዝ ከነበረ የሕዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪ ጋር ቀሲም ቀበሌ ላይ በመጋጨታቸው መሆኑ ተገልጿል፡፡

በዚህም የአራት ሰዎች ሕይወት ወዲያውኑ ሲያልፍ በ14 ሰዎች ላይ ከባድ እንዲሁም በስምንት ሰዎች ላይ ቀላል የአካል ጉዳት መድረሱን ከወረዳው ኮሙኒኬሽን ጽ/ቤት የተገኘው መረጃ አመላክቷል፡፡

የአደጋው መንስዔም በፍጥነት ማሽከርከር እና ቅድሚያ አለመስጠት መሆኑ ተጠቅሷል፡፡