Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ሰሜን ኮሪያ ወደ ምስራቅ ባህር ባላስቲክ ሚሳዔል ማስወንጨፏ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 14፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ሰሜን ኮሪያ ወደ ምስራቅ ባህር ባላስቲክ ሚሳዔል አስወንጭፋለች ሲሉ የደቡብ ኮሪያ የጥምር ኃይል አዛዥ አስታወቁ፡፡

ሀገሪቱ ሚሳዔሉን ያስወነጨፈችው ሃዋሳል-1 አር ኤ-3 የተሰኘውን ስትራተጂካዊ የክሩዝ ሚሳኤል አቅምን እና አዲሱን ፒዮልጂ-1-2 ፀረ-አውሮፕላን ሚሳዔል ሙከራ ካደረገች ከሦስት ቀናት በኋላ መሆኑም ተመላክቷል፡፡

ባለስቲክ ሚሳዔሎች በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት ቁጥጥር የሚደረግባቸው ቢሆንም በዚህ ወር መጀመሪያ ላይ ብቻ የመካከለኛ ርቀት ሃይፐርሶኒክ ሚሳዔል ሙከራ ከተጀመረ 20 ቀናት ማለፋቸውን ተናግረዋል።

ይሁንና የጥምር ኃይሉ አዛዥ የተወነጨፈው ሚሳዔል የበረራ ርቀቱን ጨምሮ የማስጀመሪያውን ዝርዝር ሁኔታ በመመርመር ላይ እንደሚገኝ መናገራቸውን ኬቢኤስ ወርልድ ዘግቧል።

Exit mobile version