የሀገር ውስጥ ዜና

ትውልዱ የአካባቢ ብክለት መንስኤ ሳይሆን የመፍትሄው አካል ወደ መሆን እየተራመደ ነው – አቶ ሽመልስ አብዲሳ

By Melaku Gedif

April 22, 2024

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 14፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የአሁኑ ትውልድ የአካባቢ ብክለት መንስኤ ሳይሆን የመፍትሄው አካል ወደ መሆን እየተራመደ ነው ሲሉ የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ ገለጹ፡፡

ርዕሰ መስተዳድሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት÷ የሰው ልጅ ከተፈጥሮ ሃብቶች ተነጥሎ ትርጉም አይኖረውም ብለዋል፡፡

አባቶች ከዚህ እውነት በመነሳት “የተፈጥሮ ሃብትን መንከባከብ ወይም መጠበቅ ሕይወትን መጠበቅ ነው” ሲሉ እንደነበርም አውስተዋል፡፡

ይህ ትውፊት በሒደት በመዘንጋቱ ከባድ ውድመት ደርሷል ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ÷ ለዚህ ደግሞ የሀራ ማያ መድረቅ ትልቅ ማሳያ መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡

የአሁኑ ትውልድ ደግሞ የብክለት ሳይሆን የመፍትሄው አካል ወደ መሆን እየተራመደ መሆኑን ነው የተናገሩት፡፡

ለዚህም ትልቁ አብነት የሀራ ማያ ዳግም ሕይወት መዝራት ነው ያሉት አቶ ሽመልስ÷ የተፈጥሮ ሃብት እድሎችን በጥንቃቄ መጠቀም እንደሚገባም አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡