ስፓርት

ሊቨርፑል ፉልሃምን አሸነፈ

By ዮሐንስ ደርበው

April 22, 2024

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 13፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በ34ኛው የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ፉልሃምን የገጠመው ሊቨርፑል 3ለ 1 አሸንፏል፡፡

ሁለቱ ቡድኖች በመጀመሪያው አጋማሽ አንድ አቻ ሆነው ወደ መልበሻ ክፍል ቢያመሩም ከዕረፍት መልስ ሊቨርፑል ባስቆጠራቸው 2 ጎሎች ፉልሃም ሽንፈት አስተናግዷል፡፡

ሊቨርፑል ማሸነፉን ተከትሎም በ74 ነጥብ ከሊጉ መሪ አርሰናል ጋር እኩል ነጥብ በመያዝ በጎል ክፍያ ተበልጦ ሁለተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል፡፡