የሀገር ውስጥ ዜና

ያለአግባብ ከተወሰደው ብር 96 ነጥብ 3 በመቶው ተመልሷል – የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ

By ዮሐንስ ደርበው

April 21, 2024

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 13፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ያለአግባብ ተወስዶ ከነበረው የብር መጠን 96 ነጥብ 3 በመቶው መመለሱን አስታውቋል፡፡

ባሳለፍነው መጋቢት ወር ከሲስተም ማሻሻያ ሥራ ጋር በተገናኘ ባጋጠመ ችግር ምክንያት 801 ነጥብ 4 ሚሊየን ብር ያለአግባብ መወሰዱን ባንኩ አስታውሷል፡፡

ከዚሁ የገንዘብ መጠንም እስከ አሁን 96 ነጥብ 3 በመቶ (771 ነጥብ 3 ሚሊየን ብር) ተመላሽ መደረጉን የባንኩ መረጃ አመላክቷል፡፡

ቀሪውን ያለአግባብ የተወሰደ ብር የማስመለስ ሥራም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ነው የተመላከተው፡፡