አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 13፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) አትሌት ቀነኒሳ በቀለ በለንደን በተካሄደው የማራቶን ውድድር ከ40 ዓመት በላይ በሆናቸው አትሌቶች ከ2019 ወዲህ ፈጣኑን ሠዓት በማስመዝገቡ አድናቆት ተችሮታል፡፡
አትሌት ቀነኒሳ የዛሬውን የለንደን ማራቶን ውድድር 2 ሠዓት ከ4 ደቂቃ ከ15 ሰከንድ በመግባት ሁለተኛ ደረጃን ይዞ አጠናቅቋል፡፡
የዓለም አትሌቲክስም አትሌቱ የገባበት ይህ ሠዓት ከ2019 ወዲህ ከ40 ዓመት በላይ በሆናቸው አትሌቶች ዘንድ ሲመዘገብ የመጀመሪያው መሆኑን በመግለጽ አድናቆቱን ገልጿል፡፡
አትሌቱ ባለፈው የፈረንጆቹ ታኅሣስ ወር ላይ በቫሌንሲያ ማራቶን ውድድር 2 ሠዓት ከ4 ደቂቃ ከ19 ሠከንድ መግባቱ የሚታወስ ሲሆን በለንደን ማራቶን ደግሞ ይህን ሠዓት በአራት ሰከንድ ዝቅ በማድረግ አሻሽሎታል፡፡