ስፓርት

አትሌት ጫላ ረጋሳ የቪዬና 2024 ማራቶንን አሸነፈ

By Tamrat Bishaw

April 21, 2024

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 13፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) አትሌት ጫላ ረጋሳ የቪዬና 2024 የማራቶን ውድድርን 2 ሠዓት ከ6 ደቂቃ ከ35 ሰከንድ በመግባት በበላይነት አጠናቀቀ፡፡

በተመሳሳይ በለንደን በተካሄደ የወንዶች የማራቶን ውድድር አትሌት ቀነኒሳ በቀለ 2 ሠዓት ከ4 ደቂቃ ከ15 ሰከንድ በመግባት ሁለተኛ ደረጃን በመያዝ አጠናቅቋል፡፡

እንዲሁም አትሌት ትዕግስት አሰፋ በለንደን የተካሄደውን የሴቶች ማራቶን ውድድር 2 ሠዓት ከ16 ደቂቃ ከ23 ሰከንድ በመግባት ሁለተኛ ደረጃን ይዛለች፡፡

በለንደን ማራቶን በሁለቱም ጾታ ኬንያውያን አትሌቶች ሲያሸንፉ በቪዬና በተካሄደው የወንዶች ማራቶን ውድድርም ኬንያውያን አትሌቶች 2ኛ እና 3ኛ ደረጃን ይዘው አጠናቅቀዋል፡፡