የሀገር ውስጥ ዜና

የሌማት ትሩፋት መርሐ ግብር አፈጻጸም ላይ ያተኮረ መድረክ በሀዋሳ ከተማ ይካሄዳል

By Amele Demsew

April 20, 2024

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 12፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በሌማት ትሩፋት መርሐ ግብር በተከናወኑ ተግባራትና የተገኙ ለውጦች ላይ ያተኮረ ሀገራዊ የምክክር መድረክ ነገ በሃዋሳ ከተማ ይካሄዳል።

በምክክር መድረኩ ለመሳተፍ የክልል ርዕሳነ መስተዳድሮች ሀዋሳ ከተማ ገብተዋል፡፡

በእንስሳትና አሣ ሀብት ልማት ምርትና ምርታማነት ላይ መሰረታዊ ለውጥ ለማምጣት ታስቦ የተቀረጸው የሌማት ትሩፋት መርሐ ግብር በሁሉም ክልሎች ተግባራዊ መደረጉ ይታወቃል።

በመርሃ ግብሩ በዋናነት እንቁላል፣ ዶሮ፣ ማር፣ ወተት እና አሣ ልዩ ትኩረት የተሰጣቸው የልማት መስኮች መሆናቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡