አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 12፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በሌማት ትሩፋት መርሐ ግብር በተከናወኑ ተግባራትና የተገኙ ለውጦች ላይ ያተኮረ ሀገራዊ የምክክር መድረክ ነገ በሃዋሳ ከተማ ይካሄዳል።
በምክክር መድረኩ ለመሳተፍ የክልል ርዕሳነ መስተዳድሮች ሀዋሳ ከተማ ገብተዋል፡፡
በእንስሳትና አሣ ሀብት ልማት ምርትና ምርታማነት ላይ መሰረታዊ ለውጥ ለማምጣት ታስቦ የተቀረጸው የሌማት ትሩፋት መርሐ ግብር በሁሉም ክልሎች ተግባራዊ መደረጉ ይታወቃል።
በመርሃ ግብሩ በዋናነት እንቁላል፣ ዶሮ፣ ማር፣ ወተት እና አሣ ልዩ ትኩረት የተሰጣቸው የልማት መስኮች መሆናቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡