የሀገር ውስጥ ዜና

130 የቅማንት የማንነት ኮሚቴ አባላት በክልሉ መንግስት የተደረገላቸውን የሰላም ጥሪ በመቀበል ወደ አካባቢያቸው ተመልሰዋል

By Tibebu Kebede

December 17, 2019

አዲስ አበባ፣ ህዳር 30፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) በአማራ ክልል 130 የቅማንት የማንነት ኮሚቴ አባላት የተደረገላቸውን የሰላም ጥሪ ተቀበለው በመግባት በአካባቢው ሠላም ዙሪያ እየመከሩ መሆኑን የክልሉ መንግስት አስታውቋል።

የአማራ ክልል የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ፅህፈት ቤት ዋና ዳይሬክተር አቶ ጌትነት ይርሳው በክልሉ ሰላም፣ ደህንነት እና እየተከናወኑ ባሉ ተግባራት ዙሪያ በዛሬው ዕለት ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል።