አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 10፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ሀገር በቀል ኩባንያዎች ተሽከርካሪዎችን እና መለዋወጫዎችን ሲያመርቱ መመልከት በእጅጉ ያበረታታል ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)ገለፁ፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው “የብረት ምርትን ማሳደግ የኢንዱስትሪ ልማት ፖሊሲያችን አካል ነው” ብለዋል፡፡
የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንትን በመጠቀም፣ ጥራት ያላቸው ከፍተኛ ኃይል አስተላላፊ የኤሌትሪክ ገመዶችን እና የኤሌትሪክ ማማዎችን ለኤሌክትሪክ ብሎም ለቴሌኮም ዘርፎች በሀገር ውስጥ ማቅረብን እየሠራንበት እንገኛለንም ነው ያሉት።
በተጨማሪም የተሽከርካሪዎችን እና የመለዋወጫዎችን የምርት ሥራ በመመልከታቸው የተሰማቸውን ደስታ የገለፁ ሲሆን÷ “ሀገር በቀል ኩባንያዎች ተሽከርካሪዎችን እና መለዋወጫዎችን ሲያመርቱ መመልከትም በእጅጉ ያበረታታል” ብለዋል።