አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 9፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በዛሬው ዕለት በሦስት በረራዎች በሳዑዲ ዓረቢያ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የነበሩ 1 ሺህ 170 ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው ተመለሱ፡፡
ከሚያዝያ 4 ቀን 2016ዓ.ም ጀምሮ እየተከናወነ በሚገኘው ዜጎችን ወደ ሀገር የመመለስ ሥራም ከ4 ሺህ በላይ ኢትዮጵያውያን መመለሳቸውን የሴቶችና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ አመላክቷል፡፡
ለተመላሽ ወገኖችም ተገቢውን ድጋፍና እንክብካቤ በማድረግ ከቤተሰቦቻቸው ጋር እንዲቀላቀሉ እየተደረገ መሆኑ ተገልጿል፡፡