Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ከድርጊታቸው በማይቆጠቡ ነጋዴዎች ላይ ሕጋዊ እርምጃ ይወሰዳል – አቶ አሻድሊ ሃሰን

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 9፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ሕገ-ወጥነትን በሚያባብሱ ስግብግብ ነጋዴዎች ላይ ክትትል በማድረግ ሕጋዊና አሥተዳደራዊ እርምጃ እንደሚወሰድ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሰ መሥተዳድር አሻድሊ ሃሰን ገለጹ፡፡

“የማዕድን ሀብታችን ለጋራ ብልጽግናችን” በሚል መሪ ሐሳብ ከተለያዩ የወርቅ አምራቾችና አዘዋዋሪዎች ጋር የንቅናቄ መድረክ ማካሄዳቸውን አቶ አሻድሊ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው አስታውቀዋል፡፡

በክልሉ የሚገኘውን የማዕድን ሀብት ትርጉም ባለው እና በዘላቂነት ለመጠቀም በዘርፉ የሚስተዋሉ ችግሮችን በጋራ ለመፍታትም ከሚመለከታቸው አካላት ጋር መምከራቸውን ነው የገለጹት፡፡

የማዕድን ሀብቱ በሕግ ካልተመራ ለኢኮኖሚ ዕድገት እንቅፋት ስለሚሆን በክልሉ የሚገኘውን የማዕድን ሀብት በዘላቂነት ለመጠቀም የሚስተዋሉ ችግሮችን በቅንጅት መፍታት እንደሚገባም ተናግረዋል፡፡

በሕጋዊ ማዕቀፍ ሕገ-ወጥነትን የሚያባብሱ ጥቂት ስግብግብ ነጋዴዎች ላይ ክትትል እየተደረገ ከድርጊታቸው በማይቆጠቡት ላይ ሕጋዊና አሥተዳደራዊ እርምጃ እንደሚወሰድም በአጽንኦት ገልጸዋል፡፡

Exit mobile version