አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 8፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ወደ ውጭ የሚላከውን የቡና ምርት መጠን ለማሳደግ አዳዲስ ገበያዎችን የማስፋት ሥራ እየተከናወነ መሆኑን የቡናና ሻይ ባለስልጣን አስታወቀ፡፡
ነባሮቹን በማስጠበቅ በመካከለኛው እና ሩቅ ምሥራቅ አዳዲስ ገበያዎች መፈጠራቸውን የባለስልጣኑ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ሻፊ ኡመር ተናግረዋል፡፡
በዚህም ውጤት መገኘቱን ጠቅሰው በቀይ ባሕር ላይ በተፈጠረው ውጥረት የተከሰተውን የኮንቴነር እጥረት እና የገበያ ጫና መቋቋም መቻሉን አንስተዋል።
በርካታ የኤስያ ሀገራትም ከኢትዮጵያ የቡና ምርት መዳረሻ ሀገራት መካከል መካተታቸውን ነው ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት የገለጹት፡፡
ሳዑዲ ዓረቢያ፣ አሜሪካ፣ ጀርመን፣ ቻይና፣ ጃፓን፣ ብሪታንያ እና አውስትራሊያ የኢትዮጵያ የቡና ዋነኛ መዳረሻ ከሆኑ ሀገራት መካከል ይጠቀሳሉ።
በአሸናፊ ሽብሩ