የሀገር ውስጥ ዜና

የምግብና ሥርዓተ-ምግብ መጓደልን ለመቀነስ እየተሠራ መሆኑ ተመላከተ

By Amele Demsew

April 12, 2024

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 4፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በግብርናው ዘርፍ ምርታማነትን ለማሳደግ ከሚደረገው ጥረት በተጓዳኝ ልማቱ ሥርዓተ-ምግብ ተኮር እንዲሆን እየተሠራ መሆኑን ግብርና ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

እንደ ሀገር የተቀመጠውን የምግብና ሥርዓተ-ምግብ መጓደል ችግር ለመቀነስ የተያዘውን ግብ ለማሳካት የግብርናው ሴክተር ቁልፍ ሚና እንዳለውም ነው የተገለጸው፡፡

የምግብና ሥርዓተ-ምግብ መጓደል ችግር በማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች ላይ የሚያሳድረውን ጉዳት በመረዳት በምግብ ንጥረ ነገር የበለፀገ፣ ደኅንነቱ የተጠበቀ፣ የተሰባጠረና በቂ የምግብ አቅርቦት ተደራሽነትና ተጠቃሚነትን ለማሻሻል በርካታ ሥራዎች እየተከናወኑ መሆኑን የሚኒስቴሩ መረጃ አመላክቷል፡፡

ምርታማነትን ለማሳደግ በሚደረገው ርብርብም የምግብና ሥርዓተ-ምግብ ጉዳይ ትኩረት ተሰጥቶት እየተሠራ መሆኑን የገለጸው ሚኒስቴሩ ÷ ይህን ከግብ ለማድረስም ሁሉም የድርሻውን እንዲወጣ ጠይቋል፡፡