Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የኢትዮ ጃፓን የፖለቲካ ምክክር መድረክ ተካሄደ

 

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 1፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ)የኢትዮጵያ እና የጃፓንን የዲፕሎማሲ ግንኙነት ለማሳደግ ሚና ያለው የፖለቲካ ምክክር መድረክ በጃፓን ቶኪዮ ተካሂዷል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ እና በጃፓን ፓርላማ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ምክትል ፕሬዚዳንት ኪዮቶ ሱጂ በጋራ በመሩት መድረክ ላይ ፖለቲካዊ ፣ኢኮኖሚያዊ እና የዲኘሎማሲ ግንኙነትን ለማጠናከር ያስቻሉ ሀሳቦች ተነስተው ውይይት ተካሂዶባቸዋል።

ኢትዮጵያ ከጃፓን ጋር ያላትን ግንኙነት የበለጠ ለማጠናከር ቁርጠኛ መሆኗን የገለፁት አምባሳደር ምስጋኑ፥ የንግድ እና ኢንቨስትመንት ትስስሮችን ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር ሀገራቱ በትብብር እንዲሰሩ ጥሪ ማቅረባቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላታክል፡፡

ኪዮቶ ሱጂ በበኩላቸው÷ ጃፓን ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን ግንኙነት የበለጠ ማሳደግ እንደምትፈልግ በመግለፅ አገሪቱ በአፍሪካ ማዕቀፍ ለሚኖራት ግንኙነት ኢትዮጵያ ወሳኝ ሚና እንዳላትም ተናግረዋል።

 

 

Exit mobile version