Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የህዝበ ሙስሊሙ መተጋገዝና የመረዳዳት እሴት ቀጣይነት ሊኖረው ይገባል-አቶ ደስታ ሌዳሞ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 1፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ህዝበ ሙስሊሙ በረመዳን ወቅት የነበረው የመተጋገዝና የመረዳዳት እሴት ቀጣይነት ሊኖረው እንደሚገባ የሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ደስታ ሌዳሞ ገለጹ፡፡

አቶ ደስታ ሌዳሞ 1 ሺህ 445ኛውን የዒድ-አልፈጥር በዓል አስመልክቶ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል ።

በመልዕክታቸው ÷ላለፉት ቅዱስ የፆም ቀናቶች የሙስሊም ማህበረብ ያለው ለሌለው በማካፈል ፣የተቸገሩትን በመርዳት ፣አቅመ ደካሞችን በመደገፍ ቅዱስ የሆነውን ኃይማኖታዊ ስርዓት በመፈጸማችሁ ምስጋና ይገባችኋል ሲሉ ተናግረዋል፡፡

ህዝበ ሙስሊሙ በረመዳን ወቅት የነበረው መተዛዘን፣የመተጋገዝና የመረዳዳት እሴቶችን ከረመዳን በኋላም ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል ሲሉ መልዕክት ማስተላለፋቸውን የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡

Exit mobile version