Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ሕዝበ ሙስሊሙ የዒድ አልፈጥር በዓልን ሲያከብር መልካምነትን በይበልጥ በማጽናት እንዲሆን ተጠየቀ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 1፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ሕዝበ ሙስሊሙ በረመዷን ወር በመደጋገፍ እንዳሳለፈው ሁሉ የዒድ አልፈጥር በዓልን ሲያከብርም መልካምነትን በይበልጥ በማጽናት እንዲሆን የአማራ ክልል ርዕሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ ጠየቁ፡፡

ርዕሰ መሥተዳድሩ ለ1 ሺህ 445ኛው የዒድ አልፈጥር በዓል የእንኳን አደረሳችሁ የመልካም ምኞት መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

በመልዕክታቸውም÷ ሕዝበ ሙስሊሙ በተባረከው የረመዷን ወር እርስ በእርስ በመደጋገፍና በመረዳዳት እንዳሳለፈው ሁሉ ታላቁን የዒድ አልፈጥር በዓል ሲያከብርም መልካምነትና ደግነት የበለጠ የሚጸኑበት እንዲሆን ጠይቀዋል፡፡

በዓሉ ለሰላም እና ልማት በአንድነት ለመትጋት ትብብርና ቅንጅት የሚጠናከርበት እንዲሆንም ተመኝተዋል፡፡

Exit mobile version