አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 1፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ባለፉት ዘጠኝ ወራት በሀገር አቀፍ ደረጃ 1 ሚሊየን 816 ሺህ 41 የንግድ ምዝገባና ፈቃድ አገልግሎቶች በኦንላይን መሠጠታቸውን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡
ለዘርፉ የተሻለ አፈፃፀም መገኘትም በእድሳት ወቅት ቅዳሜና እሁድን ጨምሮ በእረፍት ቀናት አገልግሎት መሠጠቱ በምክንያትነት ተጠቅሷል፡፡
በሀገር አቀፍ ደረጃ በአጠቃላይ በኦንላይን እና በባክ ኦፊስ 2 ሚሊየን 34 ሺህ 787 የንግድ ምዝገባና ፈቃድ አገልግሎት መሠጠቱን የሚኒስቴሩ መረጃ አመላክቷል፡፡
ከተሠጡት አገልግሎቶች መካከልም÷ አዲስ የንግድ ምዝገባና የንግድ ፈቃድ፣ የንግድ ፈቃድ እድሳት፣ ማሻሻያ፣ የንግድ ስም እንዲሁም መሠል 19 የተለያዩ አገልግሎቶች እንደሚገኙበት ተጠቅሷል፡፡
በ2016 በጀት ዓመት በሀገር አቀፍ ደረጃ 2 ነጥብ 8 ሚሊየን የንግድ ምዝገባና ፈቃድ አገልግሎት በኦንላይን ለመስጠት ታቅዶ እየተሠራ መሆኑም ተመላክቷል፡፡