አዲስ አበባ፣ መጋቢት 30፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በጋምቤላ ክልል ሰሞኑን ተከስቶ በነበረው የፀጥታ ችግር በመንግስትም ሆነ በፓርቲ የተሰጣቸውን ተልዕኮ በአግባቡ አልተወጡም ያላቸውን 4 ከፍተኛ አመራሮች ከሃላፊነት ማንሳቱን የክልሉ መንግስት አስታወቀ።
የክልሉ መንግስት እንደገለፀው÷ ከሃላፊነታቸው የተነሱት ሶስቱ የክልል አመራሮች ሲሆኑ አንዱ ደግሞ የዞን አመራር ነው፡፡
በዚህ መሰረትም፡-
1ኛ. የክልሉ ፍትሕ ቢሮ ኃላፊ አቶ አኳይ ኡቡቲ፣
2ኛ. የክልሉ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ አቶ ቾል ኩን፣
3ኛ. የክልሉ ገጠር መንገዶች ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ ቢተው ዳክ እና
4ኛ. የኑዌር ብሔረሰብ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ ቤት ኃላፊ አቶ ቡኝ ኜል ከሃላፊነታቸው ተነስተዋል።
የክልሉ መንግስትና ፓርቲው የሰጣቸውን ሃላፊነት መወጣት ባልቻሉ አመራሮች ላይ እየተወሰደ ያለው እርምጃ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል መገለጹንም የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡