አዲስ አበባ፣ መጋቢት 30፣ 2016 (አፍ ቢ ሲ) በአማራ ክልል ምዕራብ ጎንደር ዞን ምድረ ገነት ከተማ፣ በሰሜን ጎንደር ዳባት ከተማ፣ በማዕከላዊ ጎንደር ዞን አርማጭሆ ከተማ፣ በደቡብ ወሎ ዞን ለገሂዳ ወረዳ ወይን አምባ ከተማ እንዲሁም በሰሜን ሸዋ ዞን እንሳሮ ወረዳ ሀገራዊ ለውጡን በመደገፍ ህባዊ ሰልፍ ተካሂዷል።
በድጋፍ ሰልፉ ለክልላችን ሰላም በህብረት እንቆማለን፣ በጥቂት ፅንፈኛ ኃይሎች አስተሳሰብና እኩይ ድርጊት የሚበተን ሀገርና ህዝብ የለንም፣ ክልላችንን በዉክልና ጦርነት ማፍረስ አይቻልም፣ እኛ ኢትዮጵያዊያን ለሀገራችን ሠላምና ሁለንተናዊ ብልፅግና የበኩላችንን እንወጣለን የሚሉ እና ሌሎች መልዕክቶች ተላልፈዋል።
የሰልፉ ተሳታፊዎች ጉድለቶችን በማረም በለውጡ የተገኙ ድሎችን አጠናክሮ ለማስቀጠል ከለውጡ አመራር ጋር በፅናት እንቆማለን ሲሉ መልዕክት ማስተላለፋቸውን የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ አመልክቷል።