ስፓርት

አርሰናል ብራይተንን በማሸነፍ የሊጉ መሪ ሆነ

By Mikias Ayele

April 06, 2024

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 28፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በ32ኛ ሣምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ አርሰናል ብራይተንን 3 ለ 0 በማሸነፍ የሊጉ መሪ ሆኗል፡፡

ምሽት 1 ሠዓት ተኩል ላይ በተደረገው ጨዋታ አርሰናል÷ በቡካዮ ሳካ፣ ካይ ሀቨርትዝ እና ሊያንድሮ ትሮሳርድ ጎሎች ብራይተንን ረትተዋል፡፡

ውጤቱትን ተከትሎም አርሰናል ነጥቡን 71 በማድረስ ሊጉን መምራት ጀምሯል፡፡

ቀደም ሲል በተደረጉ ጨዋታዎች ኒውካስል ፉልሃምን 1 ለ 0፣ ሉተን ታወን ቦርንማውዝን 2 ለ 1፣ ዌስትሃም ዎልቭስን 2 ለ 1 እንዲሁም ኤቨርተን በርንሌይን 1 ለ 0 ሲያሸንፉ÷ አስቶንቪላ ከብሬንት ፎርድ 3 አቻ ተለያይተዋል፡፡